አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በወሎ ዩኒቨርስቲ የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት ካምፓስ ማህበረሰብ “ደሜን በደሙ ሀገር እያስከበረ ላለው መከላከያ ሰራዊት” በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ ኘሮግራም እያካሄደ ነው።
የ4ኛ ዓመት የኢንጂነሪንግ ተማሪ የሆነው ኢብራሒም እንድሪስ ደሙን ሲለግስ ይህ የመጀመሪያው እንዳልሆነ ገልፆ የዛሬው ለየት የሚያደርገው የሀገርን ክብር ለማስከበር እየተዋደቀ ላለው የመከላከያ ሰራዊት በመሆኑ ስሜቱ ልዩ ነው ብሏል፡፡
ዶክተር መላኩ ታመነ በወሎ ዩኒቨርሰቲ የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቱዩት ሳይንትፊክ ዳይሬክተር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተና ገሩት የዛሬው የደም ልገሳ መርሐ ግብር በዩንቨርስቲው የሚገኙ ተማሪወች መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች በፈቃደኝነት ያደረጉት ነዉ ብለዋል።
ዪንቨርሲቲው የህወሓት ጁንታ ስር እስከሚበጣጠስ ድረስ ለመከላከያ እና ልዩ ኃይል አባለት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው የገለፁት፡፡
በእሸቱ ወ/ሚካኤል
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!