የሀገር ውስጥ ዜና

በድሬዳዋ የአንድ ቀበሌ ሴቶች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት 758ሺህ ብር ድጋፍ አደረጉ

By Meseret Awoke

August 19, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ድሬዳዋ አስተዳደር የሣቢያን ቀበሌ ሴቶች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት 758 ሺህ ብር በጥሬ ገንዘብ እና በዓይነት ድጋፍ አደረጉ።

በድጋፍ ርክክቡ ሥነ-ሥርዓት ላይ የቀበሌው ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድማገኝ በሻህ እንዳሉት÷ የቀበሌው ሴቶች ለሠራዊት ድጋፍ ካደረጉት መካከል በራሳቸው ተነሳሽነት ያዘጋጁት 146 ከረጢት በሶ ይገኝበታል።

እንዲሁም 110 ካርቶን ቴምር ፣ ፓስታ፣ ሩዝና ዘይት በድጋፉ ውስጥ እንዳሉበት ገልጸው÷ በጥሬ ገንዘብ ደግሞ 100 ሺህ ብር መለገሳቸውን አሰታውቀዋል።

በድጋፉ ከተሳተፉ ሴቶች መካከል ወይዘሮ አለምዘውድ ገሰሰ ለኤዜአ በሰጡት አስተያየት÷ ካስፈለገ ግንባር ድረስ በመዝመት ያዘጋጀነውን ምግብ ሰርተን በማቅረብ ለመደገፍ ዝግጁ ነን” ብለዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር የሠራዊቱ ገቢ አሰባባሰቢ ኮሚቴ አባል አቶ ገበየሁ ጥላሁን የዓይነትና የገንዘቡን ድጋፍ በአካባቢው ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ተወካይ ኮሎኔል ዮናስ ሮባ አስረክበዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደርና ነዋሪዎቹ ሀገርን ለማዳን እያደረጉ የሚገኙትን ድጋፍ እስከመጨረሻው እንደሚያጠናክሩ አቶ ገበየሁመልዕክት አስተላልፈዋል።

ኮሎኔል ዮናስ በበኩላቸው ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው÷ ደጀን የሆነው ህዝብ ለሠራዊቱ የሚሰጠው ፍቅር፤ ክብርና ድጋፍ ሀገር የማዳን ተልዕኮውን እንዲወጣ እንደሚያስችሉ ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!