የሀገር ውስጥ ዜና

አሸባሪውን የሸኔ ቡድን  የሚያወግዙ  ሰልፎች በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች እየተካሄዱ ነው

By Meseret Demissu

August 20, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 14 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሸባሪውን የሸኔ ቡድን  የክህደት ተግባር የሚያወግዙና ለሀገር ህልውና የተሰለፈውን ሰራዊት የሚደግፉ ሰልፎች በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞችና ዞኖች እየተካሄዱ ነው።

በየከተሞቹ የሚገኙት የኤፍ ቢ ሲ እና የኦቢኤን  ሪፖርተሮች እንደዘገቡት በአሰላ፣ በአምቦ ፣ በሆለታ፣ በወሊሶ፣ በዱከም፣ በገላንና በሌሎች  ከተሞችና አካባቢያቸው የሚገኙ ነዋሪዎች ባካሄዱትት ሰልፍ የሸኔ የሽብር ቡድን  ከወያኔ ጋር የፈጠረው ጥምረት ከሃዲነቱን በድጋሜ ያረጋገጠበትና  ለኦሮሞ ህዝብ ያለውን ንቀት ያሳየበት ድርጊት ነው ብለዋል።

ሰልፈኞቹ ‘’የሃገራችን ብልፅግና በውስጥና በውጭ ጠላቶቻችን አይደናቀፍም፣ ወያኔን ባስወገደው የተባበረ ክንዳችን ሸኔን እንነቅላለን፤  ሸኔ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት ነው’’ የሚሉና ሌሎች  መልዕክቶችን አስጋብተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!