አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 14 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የድሬደዋ ዩኒቨርስቲ በወሎ ዩኒቨርስቲ ተጠልለው ለሚገኙ ተፈናቃዮች የዕለት ደራሽ ምግቦችና ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጓል።
አሸባሪው የህዉሓት ቡድን የከፈተውን ጥቃት ተከትሎ፥ በወሎ ዩኒቨርሲቲ ተጠልለው ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ እንዲደረግ ዩኒቨርስቲው ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ድጋፍ ዛሬ ወደ ስፍራው ልኳል።
ለተፈናቃዮቹ ምግብ ነክ የሆኑና ያልሆኑ የተለያዩ ድጋፎች መደረጋቸውን የገለፁት የድሬደዋ ዩቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዑባህ አደም፥ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ዩኒቨርስቲው በቀጣይም በጦርነቱ ምክንያት ከተለያዩ ከአፋርና አማራ ክልል ለተፈናቀሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!