የሀገር ውስጥ ዜና

ሶማልያ የኢትዮጵያ የወጪ ምርቶች መዳረሻ በመሆን ቀዳሚውን ስፍራ ያዘች

By Meseret Demissu

August 20, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 14 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ2013 በጀት ዓመት ኢትዮጵያ የግብርና፣ የማዕድንና የማኑፋክቸሪንግ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ 3 ነጥብ 62 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር አግኝታለች፡፡

ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ ይህን ያህል ገቢ ያገኘችው ምርቶቿን ወደ 136 አገራት በመላክ ነው፡፡

ከወጪ ምርት ገቢ 347 ነጥብ 83 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ በማስገኘት ሶማልያ ከኢትዮጵያ ወጪ ምርቶች መዳረሻ አገራት ቀዳሚውን ስፍራ ይዛለች፡፡

በ2012 በጀት ዓመት 320 ነጥብ 16 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በማስገኘት የዕቅድ አፈፃፀሙን 10 ነጥብ 57 በመቶ ድርሻ ቀዳሚውን ስፍራ የዛ የነበረችው ኔዘርላንድ በ2013 በጀት ዓመት ኔዘርላንድ 344 ነጥብ 94 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር፣ የናይትድ ስቴትስ 293 ነጥብ 32 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በማስገኘት እንደቅደም ተከተላቸው የሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

የ2013 በጀት ዓመት ከወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ ከ2012 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ19 ነጥብ 5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ጭማሪ ማሳየቱን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!