አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ትራንስፖርት ባለስልጣንና ተጠሪ ተቋማት እንዲሁም በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ9 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ።
በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ በአዳማ ከተማ በተካሄደው ውይይት ወቅት የኦሮሚያ ትራንስፖርት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልቃድር ሁሴን ÷በሀገር መኖር፣ ሠርቶ ማግኘትና ነግዶ ማትረፍ የሚቻለው ሰላም ሲኖር ብቻ ነው ብለዋል፡፡