የሀገር ውስጥ ዜና

የቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የ3 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

By Meseret Demissu

August 22, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀብሪደሃር  ዩኒቨርሲቲ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት 3 ሚሊየን ብር ገንዘብ በማሰባሰብ ድጋፍ አደረገ ።

ዩኒቨርሲቲው በተጨማሪም 3 መቶ ፍየሎችን አስረክቧል።

የቀብሪደሃር ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች አገልግሎት ሀላፊ አቶ ዳንኤል ግርማ ፣ የሽብር ቡደኑ እስከሚደመስሰ ደረስ ድጋፍ በማድረግ ደጀንነቱን እንቀጥላለን ብለዋል ።

የመከላከያ ፋይናንስ ስራ አመራር ዘርፍ ተወካይ ብ/ጀ አለምሰገድ ወንድወሰን በበኩላቸው፥ የኢትዮጵያ ህዝብ አዲስ ምልምል ሰልጣኞች ወደ ማሰልጠኛ በመላክና ድጋፍ በማድረግ ሀገራዊ ግዴታውን እየተወጣ መሆኑን ገልፀው ፣ የቀብሪደሃር ዩኒቨርስቲ ላደረገው ድጋፍም ማመስገናቸውንከመከላከያ ሰራዊት የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!