አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ በሰሜን ኢትዮጵያ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ምግብ ነክ ፣ የቤት ቁሳቁሶች እና አልባሳትድጋፍ አደረገ።
ዩኒቨርስቲው ድጋፋ ያደረገው ተማሪዎቹን ፣ መምህራን የአስተዳደር ሰራተኞችና የቤጅንግ አጠቃላይ ሆስፒታልን በማስተባበር ነው።
የተደረገው ድጋፋ ከአንድ ሚሊየን ዘጠኝ መቶ አርባ ሶስት ብር በላይ ይገመታል ያሉት የዩኒቨርሲቲው ንብረት አስተዳደር ዳሬክተርና የድጋፋ አስተባባሪ አቶ መለሠ ዘውዴ፥ በዚህ ወቅት ኢትዮጵያዊነት በችግር ውስጥ አብቦ ሲያፈራ አይተናል ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አገልግሎት ዳሬክቶሬት ዳሬክተር ዶክተር ሠለሞን ተስፋዬ በበኩላቸው፥ ይህ የዩኒቨርስቲዎች ትብብር ወደ ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት የሚያድግ ነው ብለዋል።
ለምግብነት አገልግሎት የሚውሉ ሩዝ ፣ድንች ፣ስኳር፣ አተር፣ ሽሮ እና ካሮት የቀረቡ ሲሆን ፥ጃኬት ሱሪ ሸሚዝ ብርድልብስ ጫማ ፎጣ ቱታና ፍራሽ ለድጋፍ የቀረቧቸው አልባሳት ናቸው።
በድጋፋ የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶች ሳፋ ብረትድስት የውሀ ጀሪካን ተካተዋል።
ድጋፋን የተረከበው የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር አጸደ ተፈራም ለዩኒቨርሲቲው ምስጋና አቅርበዋል።
በአለባቸው አባተ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!