የሀገር ውስጥ ዜና

መንግሥት ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ያለው ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው – የዩኒሴፍ የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር

By Meseret Demissu

August 23, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከተመድ የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር መሃመድ ማሊክ ፎል ጋር  ተወያይተዋል።

ውይይታቸውም በወቅታዊና ሰብአዊ ጉዳዮች እንዲሁም ያጋጠሙ ተግዳሮቶች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተመላክቷል።

ዳይሬክተሩ ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ እያከናወነ የሚገኘው የሰብአዊ ዕርዳታ ተግባራት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ ያለውን ቁርጠኝነት ማድነቃቸውን የሰላም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!