የሀገር ውስጥ ዜና

የአሸባሪውን ቡድን ፍጻሜ በአጭር ጊዜ ለማድረግ ተነስተናል – የወሎ ግንባር ዘማቾች

By Meseret Awoke

August 23, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪውን ቡድን ፍጻሜ በአጠረ ጊዜ ለማድረግ መነሳታቸውን በወሎ ግንባር የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የክልል ልዩ ሀይሎችና ሀገርን ለማዳን የዘመቱ ታጣቂዎች ተናገሩ፡፡

ከሚወዷት ሀገራቸውና ከሚሳሱለት ህዝብ በተቃራኒ የቆመውን አሸባሪ ቡድን ለመደምሰስ በቂ ዝግጅት እንዳላቸው ገልጸዋል።

የወቅቱ የአየር ፀባይ፣ መልክዓምድርና የቤተሰብ ሁኔታ ያልበገራቸው የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ አሸባሪውን ቡድን እየደመሰሱት ይገኛሉ።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ግንባር ድረስ በመዝለቅ ሁኔታውን ተመልክቷል።

በዚህም የጠላትን ፍፃሜ ለማድረግ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የክልል ልዩ ሀይሎች፣ ሚሊሻዎችና ሌሎች ታጣቂዎች በጋራ እየሰሩ ድንቅ ገድልም እያስመዘገቡ መሆኑን ታዝቧል።

በየአካባቢው በእናቶች የተዘጋጁ ስንቆች ለጀግኖቹ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ብርታት የሆናቸው ሲሆን÷ የሰራዊቱ አባላት ይህ ለበለጠ ድልና አሸናፊነት እንዳዘጋጃቸው ተናግረዋል።

የሰራዊቱ አባላትም ለጠላት ያልተራዘመ ጊዜ በመስጠት በአጠረ ጊዜ የጁንታውን ፍፃሜ ለማድረግ መነሳታቸውን ያስረዳሉ።

ከዚህ ቀደም የመከላከያ ሰራዊት አባል በመሆን ሃገር ሲያገለግሉ የነበሩ አባላት በድጋሚ ሰራዊቱን በመቀላቀል ጠላትን እየደመሰሱ ይገኛሉ።

በአፈወርቅ እያዩና ለይኩን ዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!