ዓለምአቀፋዊ ዜና

ታይዋን ያመረተችውን ሀገር በቀል የኮቪድ19 ክትባት ለዜጎቿ መስጠት ጀመረች

By Alemayehu Geremew

August 23, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ታይዋን ያመረተችውን ሜዳይጀን የተሰኘ የኮቪድ19 ክትባት ለዜጎቿ መስጠት ጀመረች፡፡

ክትባቱ ከዓለም ጤና ድርጅት ሙሉ ፈቃድ እንዲያገኝ እየተሰራ መሆኑን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ክትባቱ በሀገሪቱ የሚስተዋለው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭት እየተባባሰ መምጣቱን ተከትሎ ጥቅም ላይ እንዲውል መደረጉን ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡

ይሁን እንጂ ሀገሪቱ ክትባቱን ለማዳረስ እያዳረገች ያለው ጥረት ዜጎች ክትባቱን ለመውሰድ ባሳዩት ጥርጣሬ እና ቸልተኝነት እክል እየገጠመው መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ይህን ተከትሎም የታይዋን ፕሬዚዳንት ዛይ ኢንግ ዌን ባሳለፍነው ሰኞ ክትባቱን በመውሰድ ዜጎች ያለምንም ስጋት ክትባቱን እንዲከተቡ አበረታተዋል፡፡

ክትባቱ የተመረተው ሜዳይጀን ቫክሲን ባዮሎጂክስ ኮርፕ በተሰኘ ሀገር በቀል ድርጅት መሆኑ ነው የተጠቆመው፡፡

ክትባቱ በፓራጓይ ሦሥተኛውን የሙከራ ጊዜ ከጨረሰ በኋላ ሙሉ በሙሉ ጥቅም ላይ እንደሚውል ተገልጿል፡፡

ምንጭ÷ቢቢሲ

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!