የሀገር ውስጥ ዜና

ህወሓት ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች ንብረት ከመዝረፍ ባለፈ መውሰድ የማይችለውን አውድሟል

By Melaku Gedif

August 23, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሽብርተኛው ህወሓት ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች ከዘረፈው ንብረት ባለፈ መውሰድ የማይችለውን አውድሟል።

የደቡብ ጎንደር ጋሳይ አካባቢ ነዋሪዎች ከፋና ብርድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷የሽብር ቡድኑ ህወሓት ታጣቂዎች ግጦሽ ውለው የሚመለሱ የቤት እንስሳትን ሳይቀር ተኩሰው መግደላቸውን ገልጸዋል፡፡

የሽብር ቡድኑ አባላት የአርሶ አደሩን ንብረት በመዝረፍ በሬ፣ በግ እና ፍየል እያረዱ ከመብላት ባለፈ መንገድ ላይ ያገኙትን እየገደሉ ማለፋቸውን ነው ነዋሪዎቹ የገለጹት፡፡

የቡድኑ አባላት ከሚያደርሱት ሰብዓዊ ጥፋት ባለፈ በማህበረሰቡ ላይ ያደረሱት ዘርፈ ብዙ ጉዳት በታሪካችን አይተነው አናውቅም ነው ያሉት፡፡

በምንይችል አዘዘው እና ዙፋን ካሳሁን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!