ዓለምአቀፋዊ ዜና

በሱዳን በጎርፍ አደጋ ከ50 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ ግብጽ የተሰማትን ሃዘን ገለጸች

By Meseret Awoke

August 24, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን ጎርፍ ባስከተለው አደጋ ከ50 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉን ተከትሎ ግብጽ ሃዘኗን ገልጻለች፡፡

በጎርፍ አደጋው እናትና ልጅን ጨምሮ የ52 ዜጎች ህይወት ማለፉን የሀገሪቱ የሲቪል መከላከያ ብሔራዊ ምክር ቤትቃል አቀባይ አብደል ጋሊል አብደል ራሂም መናገራቸውን ኢጂብት ቱዴይ ዘግቧል።

ሱዳን አና ግብጽ ከኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር ተያይዞ የውሃ እጥረት ያጋጥማል በማለት ተደጋጋሚ ቅሬታ እንደሚያቀርቡ ይታወቃል፡፡

በአንጻሩ በቀጠናው በቂ የውሃ አቅርቦት መኖሩን ተከትሎ ሱዳን በተደጋጋሚ ለጎርፍ አደጋ እየተጋለጠች መሆኑን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!