የሀገር ውስጥ ዜና

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ

By Meseret Awoke

August 24, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ ከ1ነጥብ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ ቁሣቁሶችን ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ።

አሸባሪው ህወሀት በአማራ እና በአፋር ክልል ባደረገው ወረራ ከሰሜኑ ወሎ አካባቢ ለተፈናቀሉ ወገኖች ነው ዩኒቨርሲቲው ድጋፍ ያደረገው። የዩኒቨርስቲው የተማሪዎች ሁለንተናዊ ልማት ተባባሪ ዲን አቶ ጌታቸው ዘውዴ ፥ይህ ወቅት ዩኒቨርሲቲዎች ሀገራዊ አንድነትን በተግባር የምናሳይበት ጊዜ ነው ብለዋል።

ለተፈናቀሉ ወገኖች አገልግሎት የሚውል 100 ከንታል ስንዴ ዱቄት፣ 500 ብርድ ልብስ፣ 500 አንሶላ እና 100 ፍራሽ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ተረክቧል።

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚንዳት ዶክተር አጸደ ተፈራ ድጋፍ ያደረጉ ዩኒቨርሲቲዎችን አመስግነዋል።

አክለውም የተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ በመሆኑ ሁለንናዊ ትብብር በሁሉም ተቋማት ዘንድ ያስፈልጋል ብለዋል።

በአለባቸው አባተ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!