የሀገር ውስጥ ዜና

የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች ለህልውና ዘመቻው ድጋፍ አደረጉ

By Alemayehu Geremew

August 24, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት በህልውና ዘመቻው ግንባር ለሚገኙት የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል እና ፋኖ የ1 ወር ደመወዛቸውን አበረከቱ፡፡

ሰራተኞቹ ÷ የሀገርን ሉዓላዊነት ለመጠበቅ ቀን ከሌት በዱር በገደሉ የሀገር ከሃዲዎችን በመተናነቅ ውድ ህይወታቸውን አሳልፈው እየሰጡ ላሉ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኃይል እና ፋኖ ነው የ1 ወር ደሞዛቸውን ማበርከታቸው የተገለፀው፡፡

በዚህም በአጠቃላይ 3 ሚሊየን 596 ሺህ 179 በላይ ብር ድጋፍ ለማድረግ መወሰናቸውን ከዩኒቨርሲቲው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ለኢትዮጵያ ክብር እየተፋለሙ ላሉት የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል እና ፋኖ በገንዘብ ብቻ ሳይሆን ደም በመለገስ፣ የዘማች ቤተሰብ ማሳን በማረም፣ እንዲሁም በተጠባባቂ ሃይልነት ራስን በማብቃት ድጋፍ እንዲያደርግ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ታምሬ ዘውዴ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!