የሀገር ውስጥ ዜና

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ተወካይ ጋር ተወያዩ

By Meseret Demissu

August 24, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከአፍሪካ ቀንድ ልዩ ተወካይ  ከዶክተር አኔቴ ዌበር ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅትም ወይዘሮ ሙፈሪያት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ  ልማት በተለያዩ መስኮች እያደረገ ለሚገኘው ድጋፍም አመስግነዋል።

ዶክተር አኔቴ ዌበር በበኩላቸው፥ የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለረጅም ዘመናት የቆየውን መልካም የዲፕሎማሲያዊ እና የልማት ትብብር ለመቀጠል ያለውን ጠንካራ ፍላጎት  መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!