የሀገር ውስጥ ዜና

በነገሌ ከተማ አሸባሪውን ሸኔ የሚያወግዝ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

By Meseret Awoke

August 25, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 19፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በጉጂ ዞን የነገሌ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ሽብርተኛውን ሸኔን በማውገዝ ህዝባዊ ሰልፍ እያካሄዱ ይገኛል።

ነዋሪዎቹ ” አሸባሪው የህወሓት ቡድን እያካሄደ ያለውን ጭፍጨፋ አንታገስም፤ ቀሬና ቄሮ የሀገር መከታ ናቸው ” የሚሉና መሰል መፈክሮችን በማስተጋባት አሸባሪ ቡድኖቹን እያወገዙ ነው።

ወጣቶች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች ጨምሮ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በሰልፉ እየተሳተፉ እንደሆነ የዘገበው ኢዜአ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!