የሀገር ውስጥ ዜና

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በጤናው ዘርፍ ያስተማራቸውን 96 ተማሪዎች አስመረቀ 

By Meseret Demissu

August 26, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 20 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 96 ተማሪዎችን ዛሬ አስመርቋል፡፡

በዛሬዉ ዕለት የተመረቁት 96 ተማሪዎች በጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስር በሚገኙ በጤና መኮንነት፣ በነርስ እና በአዋላጅ ነርስነት  ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት  ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!