የሀገር ውስጥ ዜና

በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመራው ልዑክ ቡድን በምስራቅ ሸዋ ዞን የአበባ  አምራች ኩባንያን ጎበኘ

By Meseret Demissu

August 26, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)  በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር  አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ ዶክተር ግርማ አመንቴ የተመራው ልዑክ ቡድን በምስራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ ሬድ ፎክስ ኢትዮጵያ የተባለ አበባ  አምራች ኩባንያን ጎብኝቷል፡፡

ፋብሪካው ለ2 ሺህ 500 ሰዎች የስራ እድል ፈጥሯል፡፡

የአበባ አምራች ኩባንያው ለአካባቢው ህብረተሰብ  ፋይዳ የሚውል የተለያየ መሰረተ ልማት በመገንባት ለአገልግሎት ማብቃቱን ከኦ ቢ ኤን  ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!