አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የደቡብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን ድጋፍ በሰላማዊ ሰልፍ እየገለጹ ነው።
ነዋሪዎቹ በዞኑ ጅንካ ከተማ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ ህይወቱን ገብሮ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከብር እየተዋደቀ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊትና ሚሊያ አባላት ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል ።
ነዋሪዎቹ የተለያዩ ድጋፎችን ያደረጉ ሲሆን ፥ድጋፉ ህወሓት የደቀነብን ስጋት እስኪወገድ ድረስ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!