አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የማሊ ጠቅላይ ሚኒስትር ቡቤዬ ማይጋ ከሰባት ዓመት በፊት ከተፈጸመው ፕሬዚዳንታዊ አውሮፕላን ግዥ ጋር በተያያዘ በቀረበባቸው የሙስና ክስ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀድሞው የፕሬዚዳንት ኢብራሂም ኬታ አውሮፕላን ግዥ ላይ ከመጠን በላይ ዋጋ በማውጣት ተሳትፈዋል የሚል ክስ ነው የቀረበባቸው ።
ጠበቃቸው በሠጠው አስተያየት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር የእስራት ዝርዝር ጉዳዮች አሁንም ግልፅ አይደሉም ብሏል።
የፕሬዚዳንቱ አውሮፕላን የተገዛው በ 40 ሚሊየን ዶላር ወይም 29 ሚሊየን ፓውንድ ሲሆን ፥ ዋጋው በጣም ውድ ነው በሚል ወቀሳ ቀርቦበት ነበር።
የአውሮፕላን ግዢው በተፈጸመበት በፈረንጆቹ 2014 ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመከላከያ ሚኒስትር ነበሩ።
ቡቤዬ ማይጋ ከ2017 እስከ 2019 ድረስ የማሊ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ማገለግላቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!