የሀገር ውስጥ ዜና

የሲዳማ ልማት ማህበር የንግድ ትርኢትና ባዛር ተጀመረ

By Feven Bishaw

August 27, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው የሲዳማ ልማት ማህበር የንግድ ትርኢትና ባዛር በሀዋሳ ከተማ ተጀምሯል።

‘ነፃነታችን ለልማታችን’ በሚል መሪ ቃል በተጀመረው ባዛር ላይ ከ200 በላይ አምራችና ነጋዴዎች ተሳትፈዋል፡፡