የሀገር ውስጥ ዜና

ከሳዑዲ አረቢያ 455 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ

By Meseret Demissu

August 27, 2021

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  ከሳዑዲ አረቢያ 455 ዜጎች ወደ አገራቸው ተመለሱ።

በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎቻን ወደ ሀገር ለመመለስ እየተደረገ ባለው ጥረት በዛሬው ዕለት ከሳዑዲ አረቢያ፣ ሪያድ 129 ህጻናት እና 326 ሴቶች በአጠቃላይ 455 ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተድርጓል።

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ተወካይ አቀባበል ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!