የሀገር ውስጥ ዜና

የሀረሪ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረጉ

By Melaku Gedif

August 27, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ አመራርና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የአንድ ወር ደመወዛቸውን ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የቢሮው አመራርና ሰራተኞች በዛሬው ዕለት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡

በዚህም ሀገርን ለማዳን ተጋድሎ እያደረገ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የክልል የጸጥታ አካላት የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለመለገስ ቃል ገብተዋል።

የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ሲያደርጉ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ከሀረሪ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!