የሀገር ውስጥ ዜና

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ 5 ሺህ 726 ተማሪዎችን ያስመርቃል

By Feven Bishaw

August 27, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በነገው ዕለት ለ13ኛ ጊዜ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 5 ሺህ 726 ተማሪዎች ያስመርቃል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በዋናው ግቢ ፣ በኦቶና ማስተማሪያና ሪፌራል ሆስፒታል እንዲሁም በታርጫ ግቢ በመደበኛ፣ በሳምንት መጨረሻ ቀናትና በምሽት መርሐ ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 3 ሺህ 304 ወንድና 1 ሺህ 964 ሴት ተማሪዎችን ነው የሚያስመርቀው፡፡