የሀገር ውስጥ ዜና

በደቡብ ክልል የስፖርታዊ እንቅስቃሴ የማጠቃለያ መርሃ ግብር ተካሄደ

By Feven Bishaw

August 29, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ‘እኔ ለሀገሬ ወታደር ነኝ’ ለሀገሬ እዘምታለሁ፣ የትም፣ መቼም፣ በምንም በሚል መርህ ሲካሄድ የነበረው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የማጠቃለያ መርሃ ግብር በዲላ ከተማ ተካሄደ፡፡

በደቡብ ክልል ስፖርት ኮሚሽን አዘጋጅነት የመከላከያ ሰራዊቱን ሲደግፍ የቆየው ስፖርታዊ መርሀ ግብር የአምስት ኪሎ ሜትር የእግር ጉዞ እና የደም ልገሳ በማድረግ የሚጠናቀቅ መሆኑን ከደቡብ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ያኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡