የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን ከቱርክ አምባሳደር ጋር   ተወያዩ

By Meseret Demissu

August 31, 2021

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን የቱርክ አምባሳደር ኢርፋን ናዚር ኦግሉ ጋር  በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱም ሁለቱ አምባሳደሮች በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል ያለውን ጠንካራ ወዳጅነት እና ስትራቴጂካዊ ግንኙነት በተመለከተ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።

በተጨማሪም አምባሳደር ይበልጣል በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ዙሪያ፣ በኢትዮጵያና ሱዳን መካከል ያለውን የድንበር ሁኔታ እንዲሁም የታላቁ ኢትዮጵያ  ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ስላለው አሁናዊ ሁኔታ ማብራሪያ መስጠታቸውን ሱዳን ከሚገኘው  የኢትዮጵያ ኢምባሲ  ያገኘነው  መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!