የሀገር ውስጥ ዜና

የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኘው የወገን ጦር ድጋፍ አደረጉ

By Tibebu Kebede

September 05, 2021

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኙት ለሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ።

ነዋሪዎቹ በማይጠብሪ ግንባር ለሚገኙት ለሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኃይል፣ ለኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ ከ1ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የአልባሳት እና የበሰሉ ምግቦችን ነው ድጋፍ አደረጉ፡፡

ድጋፉን ያስረከቡት የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ተወካይ አቶ ሙሉቀን ሲሳይ እንደተናገሩት፣ 8ሺ እንጀራ፣ 4ሺ ካናቴራ፣ 2ሺ ጫማ፣ 5ሺ ካልሲ እና ፓንት፣ 4 ኩንታል ቴምር እንዲሁም 5 መቶ ደርዘን እሽግ ውኃዎችን ድጋፍ አድረገዋል ፡፡

ድጋፉን የተረከቡት በአካባቢው የሚገኝ የሠራዊት ክፍል አመራር ፣ አሁን በአሸባሪው የህውሓት ቡድን ላይ እየተቀናጀን ያለነው ድል የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎናችን በመሆኑ ጭምር ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ:- የሀገር መከላከያ ሠራዊት የፌስቡክ ገጽ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!