የሀገር ውስጥ ዜና

437 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ሃገራቸው ተመለሱ

By Feven Bishaw

September 06, 2021

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሳዑዲ አረቢያ ጂዳ 84 ህጻናትን ጨምሮ 437 ዜጎች ወደ ሃገራቸው መመለሳቸው ተገለፀ፡፡

ተመላሾቹ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል ተወካይ አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡