የሀገር ውስጥ ዜና

ጅማ ዩኒቨርሲቲ የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ መርሃ ግብር አስጀመረ

By Alemayehu Geremew

September 07, 2021

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጅማ ዩኒቨርሲቲ የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት አስጀምሯል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የ16 አቅመ ደካማ ቤቶች የማደስ መርሃ ግብሩን ነው ዛሬ በከተማዋ ቦሳ አዲስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ያስጀመረው፡፡

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጀማል አባ ፊጣ እንደገለፁት÷ ዩኒቨርሲቲው በጅማ ከተማ የ10 አቅመ ደካማ መኖሪያ ቤቶችን ለማደስ አቅዶ ወደ ስራ የገባ ሲሆን÷ በቀርሳ ወረዳ ሰርቦ ከተማ ደግሞ የ6 አቅመ ደካማ መኖሪያ ቤቶች ይታደሳሉ፡፡

በተጨማሪም በክረምቱ የአረንጓዴ አሻራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ተሳታፊ በመሆን ከ 100 ሺህ በላይ የቡና እና የተለያዩ ችግኞችን በማቅረብ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር መተከሉን አንስተዋል፡፡

ዶ/ር ጀማል ለሀገር መከላከያ ሰራዊት በ 2 ዙር የ23 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውንም ገልፀዋል፡፡

በተመስገን አለባቸው