አዲስ አበባ፣መስከረም 11፣2024 (ኤፍ ቢሲ) በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ የተገነባው የአየር ትራፊክ መቆጣጠሪያ ታወር ግንባታ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የታወሩ መገንባት በጂንካ አየር ማረፊያ አማካይነት የሚሰጠውን የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ቀልጣፋ÷ ዘመናዊና ደህንነቱ የተረጋገጠ በማድረግ ረገድ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ትራንስፖርት ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ካሳሁን ጎፌ ተናግረዋል፡፡