የሀገር ውስጥ ዜና

በድንጋይ ያባረርነው አሸባሪው ህወሓት እኛ እያለን ሀገራችንን አያፈርስም – የአርሲ ዞን ወጣቶች

By Meseret Awoke

September 22, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በድንጋይ ያባረርነው አሸባሪው ህወሓት እኛ እያለን ዳግም የኦሮሚያን መሬት አይረግጥም፤ ሀገራችንንም አያፈርስም ሲሉ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የተቀላቀሉ የአርሲ ዞን እና የአሰላ ከተማ ወጣቶች ተናገሩ።

የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ለተቀላቀሉ የአርሲ ዞን እና የአሰላ ከተማ ወጣቶች የጀግና ሽኝት ተደርጎላቸዋል።

እንደ ኦቢኤን ዘገባ ወጣቶቹ በፈቃዳቸው መከላከያን ለመቀላቀል የወሰኑት ሀገርን ለማፍረስ የሚንፈራገጡትን ኃይሎች በአጭር ጊዜ ወደ ቦታቸው ለመመለስ መሆኑን ተናግረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!