አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮ-ቴሌኮም በማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን ከተሞች የ4ጂ ኤልቲ ኢ አድቫንስድ አገልግሎትን በነገው ዕለት ያስጀምራል።
አገልግሎቱ በደብረ ብርሀን፣ ፍቼ፣ ሸዋሮቢት፣ ሱልልታ፣ ሰንዳፋ፣ ገርባ ጉራቻና ለገጣፎ ከተሞች ነው የሚጀምረው።
ይህንን አገልግሎት ለማስጀመር የኢቲዮ ቴሌኮም ዋና ስራ ስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬሂወት ታምሩ ዛሬ ደብረብርሃን ከተማ ገብተዋል።
ወደ ከተማው ሲገቡም የደብረብርሃን ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ደስታ አዳርጌን ጨምሮ የከተማውና የዞን አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የአራተኛው ትውልድ ኔትዎርክ በአካባቢው መጀመሩ የኢንተርኔት አገልግሎቱን ፈጣንና ቀልጣፋ ያደርገዋል ተብሎ ይታመናል።
በአበበ የሸዋልዑል
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!