የሀገር ውስጥ ዜና

ለመከላከያ ሠራዊት የማደርገውን ድጋፍ አጠናክሬ እቀጥላለሁ- የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት

By Alemayehu Geremew

September 22, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመከላከያ ሠራዊት በተደረገው የኃብት ማሰባሰብ ድጋፍ ለጨረታ የቀረበውን ምስል የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት በግማሽ ሚሊየን ብር ዋጋ ጨረታዉን አሸንፏል፡፡

የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን ታደሰ ምስሉን መልሰዉ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት በስጦታ አበርክተዋል፡፡

ዛሬ በተካሄደዉ መርሃ ግብር ለመከላከያ ሰራዊቱ አጋርነትን የሚገልጹ ዝግጅቶች ተካሂደዋል፡፡

የኤግዚቢሽን ማዕከል እና የገበያ ልማት ድርጅት ከዚህ ቀደም 2 ሚሊየን ብር ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን÷ የድርጅቱ ሰራኞችም የአንድ ወር ደሞዛቸዉን ለመከላከያ ሰራዊት አበርክተዋል፡፡

ሀገርን ለማዳን መስዋዕት እየሆነ ላለዉ የመከላከያ ሰራዊት በቀጣይ በተቋሙ በኩል የሚደረገዉ ድጋፍ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን ታደሰ መናገራቸውን ከኤግዚቢሽን ማዕከልና ገበያ ልማት ድርጅት ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል፡፡