የሀገር ውስጥ ዜና

አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ ልትጥል ያሰበችውን ማዕቀብ ቻይና ተቃወመች

By Tibebu Kebede

September 22, 2021

 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ልትጥል ያሰበችውን አዲስ ማዕቀብ እንደምትቃወም ቻይና አስታወቀች፡፡

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሊጂያን ዣዎ ፥አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ለመጣል ያሰበችው ማዕቀብ ቻይና ትቃወማለች ብለዋል በቲውተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፡፡

አሜሪካ በጥንቃቄ ገንቢ ሚናዋን ትወጣለች ብለን እናምናለንም ብለዋል ቃል አቀባዩ፡፡

ኢትዮጵያውያን ልዩነቶችን ለመፍታት፣ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር፣ ሠላምና ጸጥታዋን ለማረጋገጥ አቅሙም ጥበቡ እንዳላት እናምናለን ብለዋል ቃል አቀባዩ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!