የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮ ቴሌኮም የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ፈጣን አገልግሎት በደብረብርሃን አስጀመረ

By Meseret Demissu

September 23, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ፈጣን አገልግሎት በዛሬው እለት በደብረብርሃን ከተማ አስጀምሯል።

በማስጀመሪያ መርሃግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬሂወት ታምሩ፥ በዛሬው እለት ይፋ የተደረገው ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ስምንት ከተሞችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል።

ደብረብርሃን ፣ ፍቼ ፣ ሸዋሮቢት ፣ ሱሉልታ ፣ ሸኖ ፣ ሰንዳፋ ፣ ገርበ ጉራቻና ለገጣፎ ከተሞች ስር የሚገኙ 386 ሺህ ያህል ደምበኞችን ተጠቃሚ ያደርጋሉም ተብሏል።

የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ፈጣን አገልግሎቱ የላቀ ፍጥነትና ባንድዊዝ እንዲሁም አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ የመረጃ ልውውጡን ፈጣን ለማድረግና የንግድ እቅስቃሴውን ቀልጣፋ ለማድረግ እንደሚያግዝም ነው ዋና ስራ አስፈፃሚዋ የተናገሩት።

ኢትዮ ቴሌኮም እስካሁን ድረስ ባደረጋቸው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ማስፋፊያ ስራዎች የዛሬውን ጨምሮ በአዲስ አበባ እና በ15 ሪጂኖች የሚገኙ 86 ከተሞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ መቻሉም ተገልጿል ።

በአበበ የሸዋልዑል

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!