የሀገር ውስጥ ዜና

ኢዜማ በአሸባሪው ህወሓት ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

By Meseret Awoke

September 23, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ /ኢዜማ/ በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ከቀያቸው ተፈናቅለው ደሴ ከተማ ለሚገኙ ዜጎች ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ አልባሳትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውለውን ድጋፍ የኢዜማ አመራርና አባላት በደሴ ትግል ፍሬ አጠቃላይ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለተጠለሉ ዜጎች እንዲውል አስረክበዋል።

የኢዜማ የሴቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል ቅድስት ግርማይ በአሸባሪው የህወሓት ወራሪ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን መደገፍ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ኃላፊነት መሆኑን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!