የሀገር ውስጥ ዜና

የትምህርት ሚኒስትሩ ጠ/ ሚ ዐቢይ የተማሩበትን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ጎበኙ

By Feven Bishaw

September 23, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ እና የልዑካን ቡድናቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቀድሞ የተማሩበትን የበሻሻ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ጎበኙ፡፡

በጉብኝታቸው ÷ ተማሪዎቹ እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሀገር ተረካቢ ለመሆን ጠንክረው እንዲማሩና ትኩረታቸውን ትምህርታቸው ላይ ማድረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡