የሀገር ውስጥ ዜና

ሀገራችንን ለአሸባሪው ቡድን አሳልፈን አንሰጥም – የመተከል ዞን ወጣቶች

By Meseret Awoke

September 23, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) “ ሀገራችንን ለአሸባሪው ቡድን አሳልፈን አንሰጥም ” ያሉ የመተከል ዞን ወጣቶች ወደ ውትድርና ማስልጠኛ አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል።

በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ የቤኒንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ግንባታና ፀጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዮት አላብሮ ፥ ምንጊዜም ከኢትዮጵያ አብራክ የተገኙ ጀግኖች ሀገራችንን አሳፍረዋት አያውቁም ብለዋል።

የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጋሹ ዱጋዝ በበኩላቸው ፥ በአሸባሪው የህወሓት ቡድን የተደቀነውን ኢትዮጵያን የማፍረ አደጋ የዞናችን ወጣቶች ከጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ጎን ተሰልፋችሁ ለመደምስ ወደ ስልጠና ስሸኛችሁ በደስታ ነው ብለዋል።

በስፍራው የሚገኘው ክፍለ ጦር አመራር በበኩላቸው ፥ እናንተ የአባቶቻቹሁን አደራ ጠባቂ ልጆች ሀገርን ያለ ማስደፈር የደም ውርስ ከጀግኖች አባቶቻችሁ ወርሳችሁ፥ አሸባሪውን ለመመከት መዘጋጀታችሁ ያኮራል ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!