የሀገር ውስጥ ዜና

አፋር ክልል የህወሓት የሽብር ቡድን በዘረጋዉ የራሱ የኢኮኖሚ ኔትወርክ ብቻ ሲዘወር ቆይቷል – ነዋሪዎች

By Meseret Awoke

September 23, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) አፋር ክልል የህወሓት ቡድን በዘረጋዉ የራሱ የኢኮኖሚ ኔትወርክ ብቻ ክልሉ ሲዘወር ቆይቷል ሲሉ ነዋሪዎች ገለፁ፡፡

የሽብር ቡድኑ ዜጎች ተረጋግተዉ እንዳይኖሩ ሲሸርብ ከቆየዉ ሴራ ባሻገር የህዝብ ሃብትን በመመዝበር ምጣኔ ሃብቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ነው የተባለው፡፡

በተለይም ‘ታዳጊ’ ብሎ በሰየማቸዉ ክልሎች ሲፈጽም የቆየዉ የሃብት ምዝበራ ምክንያት ነዋሪዎች ተገቢዉ መሰረተ ልማት እንዳይሟላላቸዉ እንቅፋት መሆኑም ይነሳል፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸዉ የክልሉ ነዋሪዎች የህወሓት ቡድን የአቅመ ደካሞችን የመሬት ይዞታ ሳይቀር በመንጠቅ ለራሱ ሰዎች ሲያድል እንደቆየም ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በህወሓት ቡድን መሬታቸዉን በግፍ ተነጥቀዉ እንደነበርና አሁን ላይ ሊመለስላቸዉ እንደቻለም አስረድተዋል፡፡

በሰመራ ከተማ በሆቴል ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማሩት አቶ መሃመድ አብደል ዋስ ÷በክልሉ ከዚህ ቀደም በኢንቨስትመንት መስክ ህጋዊ መሰማራት እና ፈቃድ ማግኘት አዳጋች እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም የህወሓት የሽብር ቡድን በዘረጋዉ የራሱ የኢኮኖሚ ኔትወርክ ብቻ ክልሉ ሲዘወር እንደቆየም አቶ መሃመድ አስታውሰዋል፡፡

የአፋር ክልል ማዕድን እና ነዳጅ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ኢብራሂም ዲሂሉ ÷በህወሓት ቡድን አላግባብ ተይዘው የነበሩ ሰፋፊ የኢንቨስትመንት እና የማእድን ስፍራዎች ተመላሽ ተደርገዋል ብለዋል፡፡

የተመለሱ መሬቶችን እና የኢንቨስትመንት አካባቢዎችን በህጋዊ መንገድ መስራት ለሚፈልጉ ዜጎች ህጋዊ መንገድን በተከተለ መልኩ እየተላለፈ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

በአወል አበራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!