የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ

By Feven Bishaw

September 24, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ በእስጢፋኖስ ቤተክርስቲያንና በአካባቢው የፅዳት ዘመቻ መካሄዱ ተገለፀ፡፡

በተካሄደው የፅዳት ንቅናቄ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ፣የፅዳት አምባሳደሮች ፣ ታዋቂ አርቲስቶች፣አትሌቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡