የሀገር ውስጥ ዜና

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የተመሰረተበትን 100ኛ ዓመት አከበረ

By Alemayehu Geremew

September 24, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የተመሰረተበትን 100ኛ ዓመት በዓሉን አከበረ።

የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሽታውን ዋለ ÷ድርጅቱ መስከረም 14 ቀን 1914 ዓ.ም በ15 የሰው ኃይልና በእጅ በሚሰራ አነስተኛ ማሽን የህትመት ስራ መጀመሩን ገልፀዋል።

በጊዜ ሂደት ድርጅቱ አሰራሩን በማዘመን ለበርካታ ሰዎች የስራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር በአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የራሱን አስተዋጽኦ ማበርከቱንም ተናግረዋል።

በዓሉ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች እስከ ጥር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ እንደሚከበር ከኢፕድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።