የሀገር ውስጥ ዜና

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር “የነጩ ፓስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግስት” ዘመቻን ተቀላቀሉ

By Feven Bishaw

September 24, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ፣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች “የነጩ ፓስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግስት” ዘመቻን ተቀላቅለዋል፡፡

የአሜሪካ መንግስት የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ፣ ሉዓላዊነትና የውስጥ አስተዳደር በማያስከብር እና የአሜሪካና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ታሪካዊና የወደፊት ግንኙነት ባላገናዘበ መልኩ በኢትዮጵያ መንግስት እና ሕዝብ ላይ የሚያደርጉትን ጫና ለመቃወም ዘመቻውን እንደተቀላቀሉ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡