የሀገር ውስጥ ዜና

የመስቀል፣ የኢሬቻ በዓላትና የመንግስት ምስረታ ስነ-ስርዓት ያለ ምንም የፀጥታ ችግር እንዲከወኑ ዝግጅት ተጠናቋል-የፌደራል ፖሊስ

By Feven Bishaw

September 24, 2021

አዲስ አበባ፣መስከረም 14፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመስቀል፣ ከኢሬቻ በዓላትና ከመንግስት ምስረታ ስነ-ስርዓት በፊትና በኋላ ሊከሰቱ የሚችሉ የፀጥታ ችግሮችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር፣ ችግር ከተከሰተ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ ከሀገር መከላከያ ሚኒስቴር፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንና ከኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮች የተዋቀሩ ጠንካራ አብይ እና ንዑሳን ኮሚቴዎች ተቋቁመው ወደ ስራ መግባታቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል መላኩ ፋንታ ገልፀዋል፡፡