የሀገር ውስጥ ዜና

በመተከል ዞን ሲስለጥኑ የነበሩ የሚሊሻ አባላት ተመረቁ

By Meseret Awoke

September 27, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመተከልን ሰላም ለመመለስ ሲስለጥኑ የነበሩ 265 የሚሊሻ አባላት ዛሬ ተመረቁ ።

በአካባቢው የሚገኛው ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ኮ/ል መልካሙ በየነ መከላከያ ሰራዊት እና በፌዴራል ፖሊስ አማካኝነት ህብረተሰቡ ራሱን እንዲከላከል እና ፀረ ሰላም ሃይሎችን ለህግ አሳልፎ እንዲሰጥ አስፈላጊው ወታደራዊ ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል ።

የግልገል በለስ ከተማ ከንቲባ አቶ ሃብታሙ ውቧልታ በበኩላቸው ፥ ከአሁን በኋላ በዞናችን ምንም አይነት የሰላም ችግር እንዳያጋጥመን ሁላችንም በቆራጥነት በመታገል የሽብርተኛውን ስራ የሚያስፈፅሙ ፀረ ሰላም ሃይሎች ማጥፋት አለብን ብለዋል ።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የክልሉ ምክትል አፈጉባኤ ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ ፣ የመተከል ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጸሃይ ጉዮ፥ ከፍተኛ አመራሮችና የጦር መኮንኖች መገኘታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!