የሀገር ውስጥ ዜና

ወ/ሮ ፈትያ አደም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባዔ ሆነው ተሾሙ

By Meseret Awoke

September 29, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ወይዘሮ ፈትያ አደም የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈጉባዔ ሆነው ተሹመዋል።

ወይዘሮ ፈትያ አደም በፉድ ኒውትሬሽን የመጀመሪያ ድግሪ ያላቸው ሲሆኑ÷ በተለያዩ የስልጣን እርከን አገልግለዋል።

አፋ ጉባዔዋ ስልጣኑን ከቀድሞ የምክር ቤቱ አፈጉባዔ ወይዘሮ ፈጡም ሙስጠፋ በተረከቡበት ግዜ የመረጣቸው ህዝብን በቅንነት ለማገልገል ቃል ገብተዋል።

ምክር ቤቱ ወይዘሮ ከሪማ አሊን በምክትል አፈጉባኤነት ሹሟል።

በእዮናዳብ አንዱዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!