የሀገር ውስጥ ዜና

በሳይንስ፣ የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ

By Meseret Awoke

September 29, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /ኢመደኤ/ እና ከደቡብ ክልል የሳይንስ፣ የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ ፡፡

የኢመደኤ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አንተነህ ተስፋዬ የደቡብ ክልል የሳይንስ፣ የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲም ወቅቱ የሚጠይቀውን ቴክኖሎጂ ለመጠቀምና የሳይበር ደህንነትን ለማረጋገጥ ከኢመደኤ ጋር በጋራ ለመስራት መወሰኑን አድንቀዋል፡፡

ኤጀንሲው ደህንነቱ የተጠበቀ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ለመዘርጋት በሚያደርገው ጥረት ኢመደኤ የበኩሉን ኃላፊነት ይወጣል ሲሉ ዶክተር አንተነህ ገልጸዋል፡፡

የደቡብ ክልል የሳይንስ፣ የኢንፎርሜሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ገቡሬ ጋጌ መስሪያ ቤታቸው ከኢመደኤ ጋር በሳይበር ደህንነት ዙሪያ በጋራ ሲሰሩ እንደነበር አውስተው÷ ተቋሙ ወቅቱ የሚጠይቀውን ዘመናዊ አሰራር ለመጠቀምና የሳይበር ጥቃት ተጋላጭነት ለመቀነስ ያግዛል ማለታቸውን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!