የሀገር ውስጥ ዜና

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በክልልነት የመደራጀት ህዝበ ውሳኔ ድምፅ እየተሰጠ ነው

By Meseret Awoke

September 30, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በክልልነት የመደራጀት ህዝበ ውሳኔ ድምፅ መስጠት በቦንጋ ከተማ በይፋ ተጀምሯል።

በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች የምርጫ ካርድ በወሰዱባቸው ምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተው ድምፅ እየሰጡ ይገኛሉ።

ኢዜአ ባደረገው ምልከታ ድምፅ የመስጠት ሂደቱም ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እየተከናወነ ነው።

የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች-ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ምዕራብ ኦሞ ዞኖች እና ኮንታ ልዩ ወረዳ “በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል” ለመደራጀት የሚያካሂዱት ህዝበ ውሳኔ ሲሆን÷ ከ 1 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ዜጎች ድምፅ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!