የሀገር ውስጥ ዜና

የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ድምጽ ሰጡ

By Meseret Awoke

September 30, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ከክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ እና የክልሉ የብልፅግና ፖርቲ ሃላፊ አቶ አብዱልጀባር መሀመድ ጋ በአቦከር የምርጫ ጣቢያ መገኘት ነው ድምፃቸውን የሰጡት።

ወይዘሮ ሚስራ አብደላ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልክት ሁሉም የክልሉ ነዋሪ ህገመንግስታዊ መብቱን በመጠቀም ምርጫውን ማከናወን ይጠበቅበታል ብለዋል።

የክልሉ ብልፅግና ፖርቲ ሃላፊ አቶ አብዱልጀባር መሀመድ በበኩላቸው ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ በሀረሪ በሰላም እየተካሄደ እንደሚገኝ ገልፀው፣ ምርጫው በሰላም ይጠናቀቅ ዘንድ ህብረተሰቡ እያሳየው ለሚገኘው ትብብር አመስግነዋል።

በእዮናዳብ አንዱዓለም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!