የሀገር ውስጥ ዜና

አሸባሪው ቡድን ሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክን ለማውደም ያደረገው ሙከራ መክሸፉ ተገለጸ

By Feven Bishaw

September 30, 2021

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ቡድን ሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክን በምሽግነት ለመጠቀምና ለማውደም ያደረገው ሙከራ በማኅበረሰቡና በጸጥታ ኃይሉ መክሸፉን የደባርቅ ከተማ ነዋሪዎችና የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጹ።

“ቱሪዝም ለሁለንተናዊ እድገት” በሚል መሪ ቃል የቱሪስት መዳረሻ የሆኑትን ቅርሶች ከጠላት መጠበቅና አሸባሪውን የትህነግ ቡድን ከሚያደርሰው ጥፋት ለመታደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ የከተማው ነዋሪዎች መክረዋል፡፡